Wednesday, May 11, 2016

እንግሊዝኛ እና የገጠር ማህበርሰብ



                     
 
       በተለይ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት ገጠሮዎች የሚኖሩት ማህበረሰብ የሚገለገሉት ማግባብያ አንዲት ናት።ለምሳሌ በተለያየ ገጠር  አፋር ካሄዴን አፋርኛ ብቻ   ነው  ትግራይም ኣንደዛ  ኣማራም  አንደዛ   አማርኛ ብቻ ናችው የሚናገሩት ከዚህ ሌላ    ቋንቋ የሚጠቀም ማህበረሰብ የለም ማለት ይቻላል ።   ባሁኑ ጊዜ አንዳንድ ወጣቶች የተማኣሩ ቢኖሩም ኣነሱም ተምረ ውጤት ካገኙ ከተማ ይገባሉ ።

     ታድያ ይህ ሆኖ ሳለ በገጠር ላይ በእንግሊዝኛ የተለያዩ ማስታወቅያዎች በብዙ አከባቢ ይተላለፋሉ  ለምሳሌ በጤና ጣቢያዎች  በትምህርት ቤቶች የሚሰሩ የጽሁፍ ማስታወቅያዎች በእንግሊዝኛ ተጽፈው እናገኛቸዋለን ።ነገር   ግን ምን አይነት ማስተዋቅያ    እንደ ተጻፈ አይቶና ሰምቶ የማያውቅ ማህበረሰብ ነው ያለው። ይህ ማስታወቅያ የተጻፈው ለገጠሩ ማህበረሰብ ነው እንጂ እዛ  ለተቀጠረ ሰራተኛ አይደለም ።

     ማስታወቅያው ስለ ምን  እንደ ሚያወራ ወይም እንደ ሚተላለፍ ለምሳሌ ስለ ወንድ ወይም ስለ ሴት በተጨማሪም ስለ ፖለቲካ ፣ኢኮኖሚ ከየት ጀምሮ መች እንደ ሚያልቅ ወዘተ የሚያውቅ ማህበረሰብ የለም ። ምክንያቱም የታወረ ማየት አይችልም እንደ ሚባለው እዛ ገጠር አከባቢ ያለ ማህበረሰብ ካለ አንድ መግባቢ ሌላ የውጭ መግባባት አይችልም ። ስለዚህ በዚህ አከባቢ በእንግሊዝኛ ማስታወቅያ መጻፍ አያስፈልግም ።

       ምክንያቱም በእንስራ ውስጥ የተለኮሰ ሻማ ሆኖ ይቀራል ። ማለትም ማህበረሰቡ ስለ ማያውቀው ተጠቃሚዎች አይሆኑም ከዚህ አንጻር ማህበረሰቡና ድርጅቱ ይጎዳሉ ።ስለዚህ አንድ ማስታወቅያ ሲሰራ የማህበረሰቡ ባህል ወግ፣መግባቢያ ፣ሀይማኖት አስቀድሞ በግምት ውስጥ ማስገባት አለበት ።                                                  

No comments:

Post a Comment